የአፋር ክልል ምክር ቤት ለ2019 በጀት ዓመት ከ33.2 ቢሊየን ብር በላይ በጀት አፀደቀ።
ምክር ቤቱ ነሐሴ 2ቀን 2019 ዓ.ም የጀመረው 6ኛ የምርጫ ዘመን፣ 5ኛ የሥራ ዘመን፣ 10ኛ መደበኛ ጉባዔውን በሰመራ ከተማ ማካሄዱን ቀጥሏል።
ረቂቅ በጀት ያቀረቡት የገንዘብ ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ደረሳ መሐመድ እንዳሉት፤ በጀቱ ከመንግሥት ድጎማ ከክልሉ የውስጥ ገቢ፣ ከፌዴራልና ከተለያዩ ሌሎች አማራጮች የሚሸፈን ነው።
ለበጀት ዓመቱ የተመደበው ገንዘብ የክልሉን ልማት ለማቀላጠፍና የሕዝቡን ጥያቄዎች ለመመለስ የሚያስችል ከመሆኑም በላይ የተጀመሩ የልማት ሥራዎችን አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚረዳ መሆኑንም አመላክተዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: