Search

የምክክር ሂደቱ ወደ ተስፋ ሰጪ ደረጃ ላይ እየደረሰ ይገኛል - ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ

ሰኞ ነሐሴ 04, 2018 52

እየተካሄደ ያለው ሀገራዊ የምክክር ሂደት ተጠናክሮ መቀጠሉን እና አበረታች ደረጃ ላይ መድረሱን የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ዋና ኮሚሽነር ፕሮፌሰር መስፍን አርዓያ አስታውቀዋል።

ዋና ኮሚሽነሩ የምክክር ጉባኤውን ሂደት አስመልክተው በሰጡት መግለጫ እንዳብራሩት፣ በአሁኑ ወቅት 250ዎቹ የምክክር ቡድኖች አጀንዳዎቻቸውን ሁለት ጊዜ በመመልከት እና በማጠናቀር 500ዎቹ ቡድኖች እያዘጋጁ ይገኛሉ።

አብዛኛዎቹ ዝግጅታቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን፣ አጠቃላይ 250ዎቹ ቡድኖች የሀሳብ ማጠናቀር ሥራ ዛሬ ማታ ሙሉ በሙሉ ይጠናቀቃል ተብሎ ይጠበቃል።

ቀጣዩ ሂደት ደግሞ 500ዎቹ ቡድኖች እነዚህን የተሰባሰቡ ሀሳቦች ይበልጥ በማዳበር ለዋናው ጉባኤ የሚያዘጋጁበት እንደሚሆን ፕሮፌሰር መስፍን ጠቁመዋል።

ይህ የሀሳብ ማጠናቀር እና የምክክር ሂደት ቀላል የሚባል እንዳልነበር ያስታወሱት ፕሮፌሰር መስፍን፣ 10 ቡድን ጀምሮ በርካታ የሀሳብ ፍጭቶች ሲደረጉባቸው መቆየታቸውን ገልጸዋል።

በተለይም በመጀመሪያዎቹ ምዕራፎች ላይ ተሳታፊዎች ያመጡት ሀሳብ እንደመጣ እንዲያልፍላቸው ይፈልጉ ስለነበር ከፍተኛ መጨቃጨቆች እና መጎራበጦች ታይተው እንደነበር አልሸሸጉም።

ይሁን እንጂ ኮሚሽኑ ውይይቶቹ በግለሰቦች ላይ ሳይሆን በሀሳብ ላይ ብቻ እንዲያተኩሩ በቅርበት እየተከታተለ እና እየተቆጣጠረ እዚህ በመድረሱ፣ በአሁኑ ወቅት ውይይቱ እየለዘበ መጥቶ ትክክለኛውን የመግባባት መሥመር ሊይዝ መቻሉን ዋና ኮሚሽነሩ አረጋግጠዋል።

በለሚ ታደሰ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: