የኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ የድህረ ምረቃ ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ምሁራንን ያካተተ የልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ የተለያዩ የቱሪዝም መዳረሻዎችን ጎብኝተዋል።
የልዑካን ቡድኑ የአብርሆት ቤተ መጽሐፍ፣ የሳይንስ ሙዚየም፣ የአራዳ ፓርክ፣ የወንዝ ዳር ልማት እና የአንድነት ፓርክን ጎብኝተዋል።
በጉብኝታቸው ባዩት የቱሪዝም ሀብት እና በአዲስ አበባ ፈጣን የልማት ጉዞ እጅግ መደነቃቸውን እንደገለጹ ከአዲስ አበባ ቱሪዝም ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
አዲስ አበባ በሚኖራቸው ቆይታም በከተማዋ የሚገኙ ሌሎች የቱሪዝም መዳረሻዎችን እና የልማት ስራዎችን የሚጎበኙ ሲሆን ጉብኝቱ የከተማዋን የቱሪዝም ሀብት በአለም አቀፍ ደረጃ ለማስተዋወቅ፣ የቱሪዝም ኢንቨስትመንት ዕድሎችን ለማስፋት እና የጋራ ትብብርን ለማጠናከር ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: