Search

የምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ መልዕክት

ዓርብ ነሐሴ 08, 2018 113

አረንጓዴ ዐሻራ - ተፈጥሮን ከመንከባከብ እስከ ሀገራዊ የምግብና ኢኮኖሚ ሉዓላዊነት!

የአረንጓዴ ዐሻራ መርሃ ግብር ችግኝ ከመትከል ወይም አካባቢን ከማስዋብ የዘለለ፣ የተፈጥሮ ሀብታችንን የመጠበቅ፣ የማልማትና የዘላቂ ልማታችንን መሠረት የማጠናከር ስትራቴጂያዊ ሀገራዊ እርምጃ መሆኑን በተግባር እያሳየ ይገኛል።

ይህ ታላቅ ሀገራዊ ንቅናቄ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖዎችን ለመቋቋም አቅማችንን ከማጠናከሩም በላይ፣ የተፈጥሮ ስነ-ምህዳራችንን በማስተካከልና በማልማት ኢትዮጵያን አረንጓዴ ምድር እያደረጋት ነው።

ባለፉት ዓመታት የተከናወኑ ተግባራትም ኢትዮጵያ በራሷ አቅምና በዜጎቿ የጋራ ጥረት የተፈጥሮ ሀብቷን መጠበቅና ማልማት እንደምትችል ያረጋገጡ፣ በአየር ንብረት ለውጥ ምላሽ ረገድ ለሌሎች ሀገራት አርዓያ የሚሆኑ የወል ስኬቶች ናቸው።

የተፈጥሮ ሀብትን መጠበቅ ለአካባቢ ጥበቃ ብቻ ሳይሆን፣ ለግብርና ምርታማነት፣ በምግብ ራስን ለመቻል እና ለኢኮኖሚያዊ ዕድገት መሠረት ነው። ለዚህም ነው አረንጓዴ ዐሻራን የምግብና የኢኮኖሚ ሉዓላዊነታችንን ለማጠናከር ዋነኛ ዘላቂ ሀገራዊ የልማት ትኩረታችን ያደረግነው።

ይህ ትውልድ የተፈጥሮ ሀብቱን በመጠበቅና በማልማት የዚህ ዘመን መሻቱን ከማሟላት ባለፈ፣ ለመጪው ትውልድ የበለጸገችና የማትበገር ኢትዮጵያን የማስረከብ ኃላፊነት አለበት።

ለነገዋ ኢትዮጵያ ጠንካራና አስተማማኝ መሰረት ለመጣል ለዚህ ደግሞ የጀመርናቸውን የተቀናጁ የአረንጓዴ ልማት ሥራዎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: