Search

ኢትዮጵያ እና ማላዊ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰትን እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በጋራ ለመከላከል የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

ዓርብ ነሐሴ 08, 2018 118

ስምምነቱን የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (/) የማላዊ የሀገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስትር ፒተር ሙኩሂቶ ተፈራርመዋል።

ኤርጎጌ ተስፋዬ (/) በዚሁ ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ ፍልሰትን በአግባቡ ማስተዳደር ከተቻለ ለማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ልማት እና ለቀጠናዊ ውህደት የሚያግዝ ቢሆንም፣ መደበኛ ያልሆነ ፍልሰት ግን በዜጎችና በሀገር ላይ ከፍተኛ ጉዳት እንደሚያስከትል አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ለፍልሰት ምንጭ፣ መጓጓዣ እና መዳረሻ ሀገር ስትሆን፣ ማላዊ ደግሞ ወደ ደቡብ አፍሪካ ለሚደረገው ጉዞ (ደቡባዊው መንገድ) ዋነኛ ኮሪደር እና ወሳኝ የመጓጓዣ መስመር ናት።

የኢዮጵያ መንግሥት በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በሚመራው ብሔራዊ ምክር ቤት እንዲሁም በጠንካራ የፖሊሲ እና የሕግ ማዕቀፎች አማካኝነት ሕገ-ወጥ ፍልሰትን ለመግታት ያላሰለሰ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም ሚኒስትሯ ገልጸዋል።

ይህ ስምምነት በሰዎች የመነገድ ወንጀልን ለመዋጋት፣ ጤናማ የፍልሰት አስተዳደርን ለማስፈን፣ ዜጎችን ለመጠበቅ እና ተጎጂዎችን ለመደገፍ የሚያስችል መሆኑን ነው የጠቆሙት።

ዶክተር ኤርጎጌ፣ ማላዊ ፍልሰተኞችን በማስጠለል፣ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ በማድረግ እና የተደራጁ ወንጀለኞችን ለፍትሕ በማቅረብ ላበረከተችው አስተዋጽኦ ምስጋና አቅርበዋል።

የማላዊ ሪፐብሊክ የሀገር ውስጥ ደኅንነት ሚኒስትር ፒተር ሙኩሂቶ በበኩላቸው፣ ይህ የመግባቢያ ስምምነት በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር እና አጋርነት ይበልጥ ማጠናከሩን ገልጸው፣ ዜጎችን ለመታደግ እና ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን ለማስቆም ማላዊ በቁርጠኝነት እንደምትሠራ ማረጋገጣቸውን ከሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: