Search

የመደመር መንግሥት፡ የሐሳብ ዘር፣ የተግባር ፍሬ ቱሪዝም፡ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና የገጽታ ግንባታ ምሰሶ

ዓርብ ነሐሴ 08, 2018 121

የዓለም አቀፍ የቱሪዝም ኢንዱስትሪ ከጉብኝት እና መዝናኛ እንቅስቃሴነት ተሻግሮ ዓለም አቀፍ ማክሮ-ኢኮኖሚን የሚያንቀሳቅስ፣ የውጭ ምንዛሬ የሚያስገኝ እና ማኅበራዊ ልማትን የሚያፋጥን ዋና ስትራቴጂያዊ ዘርፍ ሆኗል።

በዘመናችን የጎብኚዎች ፍላጎት ወደ ጥራት፣ የተፈጥሮ ጥበቃ እና ከአካባቢ ማኅበረሰብ ጋር ጥልቅ ግንኙነት ወደሚፈጥሩ ዘላቂ ልምዶች ተቀይሯል።

በዚህም ረገድ በዓለም አቀፍ ደረጃ እንደ ፈረንሳይ እና ስፔን፤ እንዲሁም በአፍሪካ ደረጃ እንደ ሞሮኮ እና ሲሼልስ የመሳሰሉት የቱሪዝም ዘርፍን ለኢኮኖሚ ዕድገት በማዋል ስኬታማ ተሞክሮ አላቸው።

ከእነዚህ ዓለም አቀፍ እና አህጉራዊ ተሞክሮዎች ወደ ኢትዮጵያ ስንሻገር ኢትዮጵያ በተፈጥሮ፣ በታሪክ፣ በመልክዓ ምድር፣ በአየር ንብረት እና በመሳሰሉት መስፈርቶች የቱሪዝም ኢንዱስትሪን በከፍተኛ ደረጃ ለማሳደግ የሚያስችል የተሟላ አቅም እንዳላት እንገነዘባለን።

አሁን ላይ ይህንን የተሟላ አቅም ከቀደምት ታሪካዊ እና ሃይማኖታዊ ቅርሶች ብቻ ከመወሰን አልፎ፣ ሰፊ የተፈጥሮ እና የኢኮ-ቱሪዝም ሀብቶችን ወደሚያካትት የተቀናጀ መዋቅር ለማሸጋገር ትልልቅ የፖሊሲ እና የኢንቨስትመንት እርምጃዎች እየተወሰዱ ነው።

በዚህ ዓለም አቀፋዊ የገበያ መዋቅር ውስጥ ኢትዮጵያ የቱሪዝም ዘርፍን ከግብርና፣ ማኑፋክቸሪንግ፣ ቴክኖሎጂ እና ማዕድን ጋር በማስተሳሰር የኢኮኖሚ ማሻሻያ ዋነኛ ምሰሶ አድርጋ እየተጠቀመችበት ትገኛለች።

ይህ ስትራቴጂያዊ እርምጃ ሰፋፊ ብሔራዊ የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶችን በማስፋፋት ዘላቂ የሥራ ዕድል ለመፍጠር ትልቅ አቅም ሆኗል። በተለይም የገበታ የመዳረሻ ልማት ፕሮጀክቶች አዳዲስ የመሠረተ-ልማት አውታሮችን በመገንባት የቱሪዝም ሥነ-ምኅዳሩን እያዘመኑት ይገኛሉ።

በወንጪ፣ ጎርጎራ እና ኮይሻ የተገነቡት ዘመናዊ የኢኮ-ቱሪዝም መዳረሻዎች ያልተነካ ተፈጥሮን ከማክሮ-ኢኮኖሚው ጋር በማስተሳሰር አሁን ያለውን ዓለም አቀፍ የቱሪስቶችን ፍላጎት የሚመልሱ ናቸው።

ቱሪዝም ከኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው ባሻገር አዎንታዊ ገጽታን ለመገንባት እና ዲፕሎማሲያዊ መስተጋብርን ለማጠናከር ከፍተኛ ሚና አለው።

እያንዳንዱ ዓለም አቀፍ ጎብኚ የኢትዮጵያን ባህል፣ ታሪክ እና የዘመናዊ መሠረተ ልማት ዕድገት በአካል ተመልክቶ ሲመለስ፣ ትክክለኛውን መረጃ ለዓለም የሚያደርስ የሕዝብ ለሕዝብ አምባሳደር ይሆናል።

ዘመናዊ አውሮፕላን ማረፊያዎች፣ የተሳለጠ የበይነመረብ ቪዛ አሰጣጥ እና ዓለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ ሎጆች መገንባታቸው ኢትዮጵያ የውጭ ጎብኚዎችን በከፍተኛ ጥራት ለማስተናገድ ያላትን ተቋማዊ ዝግጁነት በተግባር ያሳያሉ።

ይህ ዓይነቱ የተቀናጀ የቱሪዝም ልማት አካሄድ አሉታዊ ትርክቶችን በመቀየር ጠንካራ፣ አሳታፊ እና በመገንባት ላይ ያለች ኢትዮጵያን ለዓለም ማኅበረሰብ በማስተዋወቅ ረገድ ወደር የማይገኝለት መሣሪያ ነው።

የኢትዮጵያን ቱሪዝም ዘርፍን በማክሮ-ኢኮኖሚያዊ ትንታኔ ስንመለከተው ፈጣን ማገገም እና ተከታታይ ዕድገት

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: