የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ ኢትዮጵያን ከገናና የዕድገትና ሥልጣኔ ታሪኳ ጋር የማስታረቅ የሕልውና ጉዳይ መሆኑን በውጭ ጉዳይ ኢንስቲትዩት የአፍሪካ ቀንድ እና የውኃ ጂኦፖለቲካ ከፍተኛ ተመራማሪ ጋሻው አይፈራም (ዶ/ር) ገለጹ።
ኢትዮጵያ ከሦስት አሥርት ዓመታት በፊት ከገናና ሥልጣኔዋ ጋር በእጅጉ የተቆራኘ የባሕር በር ባለቤት እንደነበረች ተመራማሪው አስታውሰዋል።
በአክሱም ሥልጣኔ ወቅትም ሆነ ከዚያ በፊት እና በኋላ በነበሩት ዘመናት፣ ኢትዮጵያ የንግድ እና የውጭ ግንኙነቷን በቀይ ባሕር ቀጣና በባሕር በር እና የወደብ አገልግሎቶች አማካኝነት ታሳልጥ እንደነበር ነው የገለጹት።
የኢትዮጵያን የባሕር በር ባለቤትነት ለማሳጣት የውስጥ እና የውጭ ባዕዳን ኃይሎች በየዘመናቱ ያልሸረቡት ሴራ እና ያልፈነቀሉት ድንጋይ እንዳልነበርም አስረድተዋል።
ታሪካዊ ጠላቶች የሚሸርቡትን ሴራ በመመከት እና በማክሸፍ፣ ኢትዮጵያ አስተማማኝ የባሕር በር ባለቤትነቷን ለሺህ ዘመናት አስጠብቃ መቆየቷን አብራርተዋል።
የከሰረው የህወሓት ቡድን እና የሻዕቢያ ስብስብ ያለምንም ተጨባጭ ማስረጃም ሆነ አመክንዮ ኢትዮጵያ የባሕር በር እንድታጣ ማድረጋቸውን ጠቅሰዋል።
በዚህም ኢትዮጵያን ከገናና ታሪክ እና ሥልጣኔዋ ጋር በእጅጉ ከተቆራኘው ቀይ ባሕር እንድትገለል መደረጉን አመልክተው፤ በሀገሪቷ ብሔራዊ ጥቅምና ፍላጎት ላይ ታሪክ ይቅር የማይለው በደል መፈጸሙን አስታውሰዋል።
በኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ላይ የተፈጸመው ክህደትም በሀገራችን ዕድገት እና ብልጽግና፣ በንግድ እና ኢንቨስትመንት፣ በገቢና ወጪ ንግድ እንቅስቃሴ ላይ እንቅፋት መፍጠሩን አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ባሕር በር አልባነት ከንግድ እና የሎጂስቲክስ አቅሟ ጋር ተያይዞ በገቢ እና ወጪ ንግድ ላይ ከፍተኛ የወደብ ኪራይ እና ሌሎች የገንዘብ ወጪዎችን እንድታወጣም እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል።
በሌላ መልኩም በምሥራቅ አፍሪካ ቀጣና የሚንቀሳቀሱ የሽብር ኃይሎች የሚፈጥሩትን የሰላም እና ደኅንነት ስጋት ለመመከት ከባሕር በር ባለቤትነት መገለሏ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ቀላል የሚባል አይደለም።
በዚህም የኢትዮጵያ የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄ የቅንጦት ሳይሆን የትውልድን መጻኢ ዕጣ ፈንታ የሚወስን የብሔራዊ ጥቅምና የሕልውና ጉዳይ መሆኑን ገልጸዋል።
የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄው የታሪክ ስብራትን የማረምና ኢትዮጵያን ከገናና ታሪክና ሥልጣኔዋ ጋር የማስታረቅ ጉዳይም ጭምር መሆኑን ተናግረዋል።
ኢትዮጵያ ቀጣናዊ የኢኮኖሚ ትሥሥርን በማጠናከር የአፍሪካን ኢኮኖሚ ውሕደት ለማሳለጥ በምታደርገው ጥረት የባሕር በር ባለቤትነትን ጥያቄውን ምላሽ ማስገኘት እንደሚያስፈልግ አስረጂ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህም ቀጣናዊ ሰላም እና ደኅንነት፣ የጋራ ዕድገት እና ብልጽግናን ማረጋገጥ የዚህ ትውልድ ሀገራዊ ኃላፊነት መሆኑንም አስገንዝበዋል።
የባሕር በር ባለቤትነት ጥያቄው ዓለም አቀፍ ቅቡልነት እያገኘ ነው ያሉት ምሁሩ፤ ለዚህም ሀገራት፣ ዓለም አቀፍ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: