በኢትዮጵያና በቻይና መካከል ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነትና የሕዝብ ለሕዝብ ትስስር ይበልጥ ለማጠናከር ያለመው የ2026ቱ የቻይና አፍሪካ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት መድረክ በአዲስ አበባ ተካሂዷል።
መድረኩ የባህልና የቱሪዝም ትውውቅ በማጎልበት ረገድ ትልቅ ሚና ያለው መሆኑ በመርሐ ግብሩ ላይ ተገልጿል። በዚሁ ልዩ ዝግጅት ላይ በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ቼን ሃይ እና የቱሪዝም ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ስለሺ ግርማ ተገኝተዋል።
በመድረኩ ላይ ኢትዮጵያ በቱሪዝም ዘርፍ ያሏትን ማራኪ መስህቦችና አስደናቂ ተፈጥሯዊ ጸጋዎች ለተሳታፊዎች በስፋት ያስተዋወቀች ሲሆን፣ ቻይና በበኩሏ የዘመናት ታሪኳን ከባህሏ ጋር አያይዛ አቅርባለች።
የዚህ መድረክ ዋነኛ ዓላማ በቱሪዝም፣ በባህልና በቴክኖሎጂ ልውውጥ መስኮች የሁለቱን ሀገራት የቆየ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ ማሸጋገር እንደሆነ ተመላክቷል።
ዝግጅቱ የሁለቱን ሀገራት ህዝቦች እርስ በእርስ በማቀራረብ ዘላቂ ወዳጅነትን ለመገንባት ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑ ታምኖበታል።
በሰናይት ሰይፉ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: