የውጭ ሀገር ዜጎች የመኖሪያ ባለቤት የሚሆኑበት አሰራር ወደ ተግባር መግባቱን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር አስታወቀ።
ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱ ከመከላከያ ሚኒስቴር፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ፣ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን እና የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ጋር በአተገባበሩ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።
በመመሪያው መሠረት ማንኛውም የውጭ ሀገር ዜጋ የመኖሪያ ቤት ባለቤት ለመሆን ሊያሟላ የሚገባው እና ለአንድ መኖሪያ ቤት የሚያስፈልግ ዝቅተኛ የገንዘብ መጠን ተዘርዝሯል።
ከዚህ በተጨማሪም በኢትዮጵያ ሊኖረው የሚችለው የቤት መጠን አንድ ብቻ ነው።
የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የኢትዮጵያ የኢንቨትመንት ተመራጭነት ለማሳደግ፣ የቤት ልማቱን ለማጠናከር፣ የስራ ዕድል ለመፍጠር ይህ እርምጃ የላቀ ፋይዳ እንዳለው አብራርተዋል።
አሰራሩ ውጤታማ እንዲሆን በተቋማት ቅንጅታዊ አሰራር ወሳኝ ነው ያሉት ሚኒስትሯ፣ ለዚህም የሚመለከታቸው ተቋማት በተጠናከረ ቅንጅታዊ አሠራር መተግበር ያስፈልጋቸዋል ብለዋል።
የተለያዩ ተቋማት አመራሮች የውጭ ዜጎችን የቤት ባለቤት የማድረግ አሠራር የውጭ ቀጥታ ኢንቨስትመንትን ለመሳብ፣ የሥራ ዕድል ለመፍጠር፣ የከተሞችን ልማት ለማፋጠን እና የቤት አቅርቦትን ለማስፋት እንደሚያግዝ ገልጸዋል።
በአባዲ ወይናይ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: