የሀገር እድገት እና ብልጽግና ትርጓሜ ለረዥም ዘመናት በመንገዶች ርዝመት፣ በግድቦች ሙሌት እና በህንጻዎች ብዛት ሲለካ ቢቆይም፣ ከእነዚህ ግዙፍ ግንባታዎች ባሻገር ጠንካራ ተቋማት እና የጋራ ትርክት ካልተገነባ የተሰራው ልማት ሁሉ አደጋ ላይ ሊወድቅ ይችላል።
ባለፉት አምስት ዓመታት የኢትዮጵያ የመደመር መንግስት ይህንን መሰረታዊ የሀገረ መንግስት ግንባታ ክፍተት ለመድፈን ስር ነቀል ሽግግር አድርጓል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ኢትዮጵያ እስከ 2050 ዓ.ም ድረስ ተግባራዊ የምታደርገውን "ግራንድ ስትራቴጂ" ይፋ ሲያደርጉ ዋነኛ
ይህም የመሰረተ ልማት ግንባታ ብቻውን የሀገርን ህልውና ሊያረጋግጥ እንደማይችልና ከሚታየው ግንባታ ጎን ለጎን ስራን በብቃት የሚያቅዱ፣ የሚመሩ እና የሚፈጽሙ ጠንካራ ተቋማት፣ ሀገራዊ ፍቅር እንዲሁም የዜጎች ስነ-ምግባር የተሟላበት ከፍተኛ መዋቅር ተናቦ መገንባት እንዳለበት የሚያሳይ ነው።
በሚቀጥሉት 25 ዓመታት ውስጥ የተሟላ ከተሜነትን በከፍተኛ ፍጥነት እውን ለማድረግ የምግብ ዋስትና ጥያቄን ሙሉ በሙሉ ወደ ታሪክነት በመቀየር የዲጂታል ኢኮኖሚ፣ የዘመናማጠንጠኛው ልማትን ከማምጣት ባለፈ ሀብትን ጠብቆ ለትውልድ ማሸጋገር በሚያስችሉ ጽኑ መሰረቶች ላይ መቆሙን ገልጸዋል። ዊ ፋይናንስ እና የሎጀስቲክስ ማዕከል የመሆን እድላችን እጅግ ሰፊ ነው።
ቴክኖሎጂን እና ዘመናዊ አሰራርን መሰረት ያደረገው ይኸው ራዕይ የህዝቡን የኑሮ ዘይቤ ሙሉ በሙሉ በመቀየር የኢትዮጵያን ብልጽግና እንደሚያረጋግጥ የሚጠበቅ ሲሆን፣ የሚገነባው ሀብትና ስልጣኔ ፍትሃዊ፣ አካታች እና ዘላቂ እንዲሆን ያስችላል።
ይሁን እንጂ ይህንን ታላቅ ሀገራዊ ራዕይ እውን ለማድረግ የውሸት እና የጥላቻ ትርክትን ወደ ጎን ትቶ በሀገር ዘላቂ ጥቅም ላይ የሚያተኩር፣ ብዝሃነትን የሚያከብር እና ስነ-ምግባርን የተላበሰ ትውልድ መፍጠር የግድ ይላል።
የ2050 ግዙፍ ስትራቴጂም ሆነ የመደመር እሳቤ ግብ ኮንክሪት ላይ የቆመች ሀገርን ሳይሆን በጠንካራ ተቋማት የተደገፈች፣ በስነ-ምግባር የታነጸች እና የጋራ ራዕይ ያላትን ኢትዮጵያ ማረጋገጥ ነው።
በበረከት ሽመልስ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: