Search

የአውስትራሊያው ፐርዝ ሚንት 521.2 ኪሎ ግራም የሚመዝነውን የዓለም ትልቁን የወርቅ ብሎክ ይፋ አደረገ

ዓርብ ነሐሴ 15, 2018 32

በአውስትራሊያ የሚገኘው ታዋቂው ፐርዝ ሚንት 521.2 ኪሎ ግራም የሚመዝን ግዙፍ የወርቅ ብሎክ በማምረት አዲስ የዓለም ሪከርድ ማስመዝገቡን ይፋ አድርጓል።

ሙሉ በሙሉ ከአውስትራሊያ ምንጭ በተገኘ ጥሬ ወርቅ የተሰራውና 99.999 በመቶ ንጽህና ያለው ይህ የወርቅ ብሎክ፣ 2024 በዱባይ ተሰርቶ የነበረውን 300 ኪሎ ግራም የወርቅ ብሎክ ሪከርድ በከፍተኛ ልዩነት ማሻሻል ችሏል።

ዘጠኝ ግዙፍ የወርቅ ማዕድን አውጪ ኩባንያዎች ጥሬ ወርቁን በማቅረብ የተሳተፉበት ይህ ፕሮጀክት፣ የአውስትራሊያን የወርቅ ማዕድን ኢንዱስትሪ ትብብርና የላቀ የብረታ ብረት ቴክኖሎጂ አቅም በዓለም አቀፍ ደረጃ በተግባር ያስመሰከረ ታላቅ ስኬት ሆኖ ተመዝግቧል።

35 በላይ ከፍተኛ ባለሙያዎች የተሳተፉበት ይህ ታሪካዊ ስራ፣ ወደ 1.5 ቶን የሚጠጋ ጥሬ ወርቅ በማዘጋጀትና በልዩ የማቅለጫ ማዕከል ውስጥ እስከ 1,400 ዲግሪ ሴልሺየስ በሚደርስ ከፍተኛ ሙቀት በማቅለጥ የተከናወነ ነው።

ከማቅለጥ፣ ከመቀረጽ እና ከመወልወል ሂደቶች በኋላ የብሎኩ የመጨረሻ ክብደት 508 ኪሎ ግራም ሆኖ የጸና ሲሆን፣ የወርቁን ጥንካሬ፣ ቅርጽና ንጽህና ለማረጋገጥም የቁጥጥር ቅዝቃዜ ተደርጎለታል።

የዓለምን ሪከርድ የሰበረው ይህ ድቅቅ የወርቅ ብሎክ በምዕራብ አውስትራሊያ በሚገኘው ፐርዝ ሚንት ... 2011 ከተሰራው 1 ቶን የወርቅ ሳንቲም ጋር ጎን ለጎን ለጎብኚዎች እይታ የሚቀርብ ይሆናል።

በሲሳይ መንግስቱ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: