Search

4 ሺህ ድምፆች፣ 4 መቶ አጀንዳዎች፣ 99 በመቶ ስምምነት፦ ኢትዮጵያ አሸንፋለች

ረቡዕ ነሐሴ 20, 2018 33

በታሪክ ማኅደር የሀገራትን ዕድል የወሰኑ እንዲሁም የመከፋፈልን ጨለምተኝነት ወደ አዲስ ብርሃን የቀየሩ ታሪካዊ ክስተቶች አሉ።

በኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን አስተባባሪነት ኢትዮጵያውያን ያስመዘገቡት አስደናቂ ስኬትም ከእነዚህ ልዩ ታሪካዊ ክስተቶች አንዱ መሆን ችሏል።

ይህ በቃላት ብቻ የማይገለጽ ይልቁንም በቁጥር፣ በእውነታ እና በጽኑ ሀገራዊ መግባባት የታተመ ታላቅ ድል ነው።

በአንድ አዳራሽ 4 ሺህ ተወካዮች ታድመው፣ 4 መቶ በላይ አጀንዳዎች ላይ በነፃነት ተወያይተው 99 በመቶዎቹ ላይ የጋራ ስምምነት ላይ መድረሳቸው በዓለም አቀፍ የፖለቲካ እና የውይይት ታሪክ ውስጥ ትልቅ ስፍራ የሚሰጠው ክስተት ነው።

እያንዳንዱ ተመካካሪ የሺህዎችን እውነተኛ ብሶት፣ ፍላጎት እና የተስፋ ድምፅ ወክሎ የተገኘበት ይህ ሕዝባዊ ጉባኤ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ባህል ወደ አዲስ ምዕራፍ ያሸጋገረ ነው።

ለዘመናት ሲከማቹ የኖሩ እና ኢትዮጵያን በፖለቲካ ሲያከፋፍሉ የቆዩ እጅግ ዐበይት እና ውስብስብ አጀንዳዎች ላይ የተመዘገበው ይህ 99 በመቶ ፍጹም ስምምነት፣ ኢትዮጵያውያን በራሳቸው አቅም ታሪካዊ ቁስሎቻቸውን ማከም እንደሚችሉ ያረጋገጠ ነው።

ይህ አሃዛዊ ስኬት ልዩነቶችን በኃይል ለመፍታት ይደረግ የነበረውን አሠራር በማስቀረት፣ በሰለጠነ ውይይት ሀገራዊ አንድነትን የመገንባት ጥበብ በተግባር የታየበት ታላቅ ማሳያ ነው።

በአጠቃላይ "ኢትዮጵያ አሸንፋለች" የሚያስብለው ይህ ውጤት፣ ኢትዮጵያውያን ተወያይተው፣ ተደማምጠውና ተስማምተው የታሪክ እጥፋት መስራት እንደሚችሉ ያረጋገጠ ነው።

ዜጎች በሰለጠነ መንገድ ልዩነቶቻቸውን አሸንፈው የጋራ ቤታቸውን በጽኑ መሰረት ላይ ለማቆም መቻላቸው ለትውልድ የሚሻገር ትልቅ የድል ብስራት ነው።

በሀና ምንዳሁን

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: