Search

በመካከለኛው እና በታችኛው አዋሽ የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመቀነስ እየተሠራ ነው

ሓሙስ ነሐሴ 15, 2017 136

በአፋር ክልልመካከለኛው እናታችኛው አዋሽ የጎርፍ አደጋ ስጋትን ለመቀነስ እየተሠራ መሆኑን በውሃናነርጂ ሚኒስቴር የአዋሽ ቤዚን አስተዳደር ጽ/ቤት ገለፀ።

በነዚህ አካባቢዎች ሰሞኑንጣለው ዝናብ መጠኑ ከፍተኛ እንደነበር የገለፁት የጽ/ቤቱ ሀላፊ ኢንጂነር አደን አብዶ፤ በኃይለኛ የውሃ ፍሰት ፈርሰው የነበሩ የጎርፍ መከላከያዎችን ከየአካባቢው ማህበረሰብ ጋር በመሆን መልሶ መጠገን መቻሉን ለኢቲቪ ተናግረዋል።

የአዋሽ ውሃ መጠን ከፍተኛ በመሆኑጎርፍ መከላከል ግብረይል ጋር በመሆን ህብረተሰቡን ወደ ከፍተኛ ቦታዎችማዛወር እንዲሁም በግብርና ሥራ ላይ ጉዳት እንዳያስከትል የመከላከል ሥራ እየተከናወነ ነው ብለዋል።

በተጨማሪም ከክልሉ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በየአካባቢው በተመደቡ ባለሙያዎች አማካይነት ለህብረተሰቡ የቅድመ ማስጠንቀቂያ መልዕክት የመስጠት ሥራዎች እየተከናወነ መሆኑን ኢንጂነር አደን ገልፀዋል

በሁሴን መሐመድ

#ኢቢሲዶትስትሪም #ኢቲቪ #አፋር #አዋሽ #ጎርፍ