Search

ሁለተኛው የጎልደን ፓንዳ አዋርድ ሊካሄድ ነው

ዓርብ ነሐሴ 16, 2017 57

በዓለማችን ታሪክ በባህል፣ በፖለቲካ፣ በኢኮኖሚ፣ በቢዝነስ፣ በትምህርትና በቴክኖሎጂ ቀደምት ከሚባሉት ከተሞች አንዷ እንደሆነች የሚነገርላት የቻይና ቤጂንግ ከተማ፥ ለሁለተኛ ጊዜ የሚካሄደውን የጎልደን ፓንዳ አዋርድን ጋዜጣዊ መግለጫ አዘጋጅታለች። 

የጎልደን ፓንዳ አዋርድ በቅርቡ ከተጀመሩ እና የመዝናኛው ኢንዱስትሪውን ቀልብ ከሳቡ የሽልማት ዝግጅቶች አንዱ ሲሆን፤ በዓለማችን ለተሰሩ ልብ-ወለድ ፊልሞች፣ ዘጋቢ ፊልሞች እና አኒሜሽን ወይም በተንቀሳቃሽ ምስል የተሰሩ ፊልሞችን በመሸለም የሚያበረታታ የሽልማት ድርጅት ነው። 

የመጀመሪያው የጎልደን ፓንዳ አዋርድ የተካሄደው በፈረንጆቹ  2023 ሲሆን፤ የፓንዳ መገኛ በሆነችው ቸንግዱ ከተማም ነበር የተካሄደው። ይህንንም ተከትሎ የሽልማቱ ስም ጎልደን ፓንዳ አዋርድ እንዲሆን ምክንያት ሆኗል። 

ሽልማቱን የሚያዘጋጁት የቻይና የትምህርትና ኪነጥበብ ማዕከል እና የሲችዋን ግዛት አስተዳደር በጋራ በመሆን ሲሆን፤ አላማውም በዓለም የሚገኙ ሕዝቦች የጋራ የሆነ ራዕይ እንዲኖራቸው ማስቻል ነው ተብሏል። 

በዛሬው ጋዜጣዊ መግለጫ ሁለተኛው ጎልደን ፓንዳ አዋርድ ስለሚያጠቃልላቸው ጉዳዮች፣ የት እና መቼ እንደሚካሄድ ተገልጿል።

በዚህም መሰረት ቦታው ልክ እንደመጀመሪያው ቸንግዱ ሲሆን በአጠቃላይ በአራት ዘርፎች ነው ውድድሩ የሚካሄደው።

ሁለተኛው የጎልደን ፓንዳ አዋርድ በመስከረም መጀመሪያ 12-13  እንደሚካሄድ የተገለጸ ሲሆን፤ በውድድር ሥነ ሥርዓቱም ላይ 126 ሀገራት በላይ ይሳተፋሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ የሽልማት ድርጅቱ ዋና ዳሬክተር እና ዳኛ ቼን ካይጅ በጋዜጣዊ መግለጫው ወቅት ተናግረዋል።

በነፃነት ክንፈ