በቅርቡ በጎርፍ የፈረሰው የጌደብ ወንዝ ድልድይ በ10 ቀናት ውስጥ በምስሉ ላይ በሚታየው መሰረት በተገጣጣሚ ብረት ተሠርቶ ለአገልግሎት ዝግጁ ሆኗል።
በደብረ ማርቆስ ባህር ባሕር ዳር መስመር አማኑኤል ከተማ የሚገኘው የጌደብ ወንዝ ድልድይ ነሐሴ 3/2017 ሌሊት በጮቄ ተራራ ዙሪያ የጣለው ከባድ ዝናብ በፈጠረው ጎርፍ ፈርሶ እንደነበር ይታወሳል።
ይህን ተከትሎ ድልድዩ በ10 ቀናት ውስጥ በተገጣጣሚ ብረት በፍጥነት ተሠርቶ ለአገልግሎት ዝግጁ መሆኑ ተገልጿል።
በአንድ ጊዜ አንድ መኪና የማስተናገድ አቅም ያለው አዲሱ የብረት ድልድይ በቅርቡ ለአገልግሎት ክፍት ይሆናል ተብሏል።
በራሄል ፍሬው
#ኢቢሲዶትስትሪም #ኢቲቪ #ምስራቅጎጃም #ጌደብድልድይ