Search

የአቪዬሽን ዘርፉ የወደፊት ተስፋዎች

ቅዳሜ ነሐሴ 17, 2017 45

የኢትዮጵያ አቪዬሽን ዩኒቨርሲቲ የወደፊቱን ትውልድ በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ በምህድስና እና ሒሳብ የትምህርት ማነፅ በሚል ተማሪዎችን ያሰለጥናል።

ከነዚህ ተማሪዎች መካከልም ከቦይንግ ቲንክታንክ ጋር በሳይንስ እና ቴክኖሎጂ፣ በምህድስና እና ሒሳብ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ትናንትና አስመርቋል።

ሰልጣኞቹ ከ28 የተለያዩ የሁለተኛ ደረጃ ትቤቶች የተውጣጡ የ11ኛ ክፍል ተማሪዎች ሲሆኑ በትምህርት ሚኒስቴር አማካኝነት የተመረጡ ናቸው፡፡ ከተመራቂዎች መካከል 50 በመቶ ሴቶች ናቸው፡፡

ባለፉት ሦስት ዓመታት በተከታታይ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተማሪዎቹ በሳይንስ እና  ቴክኖሎጂ ዘርፍ የላቀ ውጤት የማምጣት ዕድላቸው የሰፋ እንዲሆን ያግዛል ተብሏል፡፡ 

ዩኒቨርሲቲው ከዚህ ቀደም በሁለት ዙሮች ከ50 በላይ የ2ኛ ደረጃ ተማሪዎችን አሰልጥኖ አስመርቋል።

 

በአሚር ጌታቸው

 #EBC #ebcdotstream #Ethiopianairlines