ወይዘሮ ኑሪያ አብዱላሂ በሐረሪ ክልል በ1992 ዓ.ም በተካሄደው ምርጫ ተመርጠው ያገለገሉ በኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት የክልል ፕሬዝዳንት ነበሩ።
ወይዘሮ ኑሪያ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለእርቅ እና ለሰላም በመሥራት የሚታወቁ እናት ናቸው።
በሐረር በበርካቶች ዘንድ ተወዳጅ የሆኑት ወይዘሮ ኑሪያ በከተማዋ ነዋሪዎች ‘አይ ኑሪያ’ የሚል መጠሪያ ተሰጥቷቸዋል። ‘አይ’ በአካባቢው ቋንቋ እናት ማለት ነው።
ከልጅነታቸው ጀምሮ አስታራቂ እንደነበሩ የሚነገርላቸው ‘አይ ኑሪያ’፤ አሁን በሀገር አቀፍ ደረጃ ስለ ሰላም የሚሰብኩ አስታራቂ ለመሆን በቅተዋል።
ማስታረቅ ከፈጣሪ የተሰጣቸው ፀጋ እንደሆነ የሚናገሩት ወይዘሮ ኑሪያ፤ ከልጅነታቸውም ጀምሮ ልጆች ሲጣሉ ያስታርቁ እንደነበር ያስታውሳሉ።
ተጣልተው ለእርቅ እሳቸው ዘንድ ከመጡ ባለትዳሮች ያልታረቁ፤ ሞት ካልለያቸው በቀርም ድጋሚ በፀብ የተነጣጠሉ አለመኖራቸውን በኩራት ይገልፃሉ።
በቢታንያ ሲሳይ
#EBCdotstream # NuriaAbdullahi #Peacemaker