Search

የመጀመሪያ 3 ነጥቡን ለማግኘት የሚጫወተው ማንችስተር ዩናይትድ

እሑድ ነሐሴ 18, 2017 50

በሊጉ መክፈቻ በሜዳው በአርሰናል 1 0 የተሸነፈው ማንችስተር ዩናይትድ 2 ሳምንት የሊጉ መርሐ-ግብር ምሽት 12:30 ላይ ከምዕራብ ለንደኑ ክለብ ፉልሀም ጋር ይጫወታል።

ፉልሀም በመጀመሪያው ሳምንት ከብራይተን ጋር ነጥብ የተጋራ ሲሆን፤ በዛሬው ጨዋታ ሁለቱም ቡድኖች የዓመቱን የመጀመሪያ ድላቸውን ለማስመዝገብ እንደሚፎካካሩ ይጠበቃል።

በክራቨን ኮቴጅ በሚደረገው ጨዋታ ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ እና ኑሳር ማዝራዊ በጉዳት የማይሰለፉ ተጫዋቾች ሲሆኑ፤ ግብ ጠባቂው አንድሬ ኦናና ከነበረበት ጉዳት ስለማገገሙ ይፋ ሆኗል።

ቀያይ ሰይጣናቱ ከሜዳቸው ውጭ በሚያደርጉት ጨዋታ ቤንጃሚን ሼሽኮ በቋሚነት ሊሰለፍ ይችላል ተብሏል።

በባለሜዳዎቹ በኩል ደግሞ ሪያን ሴሲኝሆ እና አንቶኒ ሮቢንሰን ጉዳት ያለባቸው ተጫዋቾች ናቸው።

በሌላ በኩል ክሪስታል ፓላስ ከኖቲንግሀም ፎረስት እና ኤቨርተን ከብራይተን በተመሳሳይ 10 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።

በሴራን ታደሰ