Search

ነገ በአንድ ጀምበር 4 ሺ 600 የአቅመ ደካማ ቤቶች ይገነባሉ - የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል

እሑድ ነሐሴ 18, 2017 42

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በነገው ዕለት በአንድ ጀምበር ጧሪ ላጡ፣ አረጋዊያን እና አቅመ-ደካሞች ለ4ሺ 600 ቤቶችን ለመገንባት ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።
የክልሉ ዋና የመንግስት ተጠሪ አቶ ገብረመስቀል ጫላ በሰጡት መግለጫ፤ ለቤት ግንባታው አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጓል ብለዋል።
ሁሉም በጎ ፈቃደኛ በነቂስ ወጥቶ በቤት ግንባታ እና እድሳት ሥራው እንዲሳተፍም ጥሪ አቅርበዋል።
በበጀት ዓመቱ በአጠቃላይ 14 ሺህ የአቅመ ደካማ ቤቶችን ለመገንባት ታቅዶ 8 ሺ 142 ቤቶችን እስከአሁን መገንባት እና መጠገን መቻሉንም ገልጸዋል።
ከዚህም መካከል 3ሺ 413 ቤቶች አዲስ የተገነቡ መሆናቸውን አስረድተዋል።
በክልሉ በ18 ዘርፎች 2.9 ሚሊዮን ዜጎች የተሳተፉባቸው የክረምት የበጎ ፈቃድ አገልግሎቶች እየተከናወኑ መሆኑን አንስተዋል።
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአጠቃላይ 4.9 ሚሊዮን ዜጎችን ተጠቃሚ ያደረጉ የክረምት የበጎ ፈቃድ ሥራዎች እየተከናወኑ ይገኛል ብለዋል።
 
 
በተመስገን ተስፋዬ