Search

ኤቨርተን በአዲሱ ስቴዲየም ብራይተንን አሸነፈ

እሑድ ነሐሴ 18, 2017 39

በ2ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ዛሬ አዲስ ባስገነባው ስቴዲየም ሂል ዲኪንሰን የመጀመርያ ጨዋታውን ያደረገው ኤቨርተን 2 ለ 0 አሸንፏል፡፡
ኒዳዬ እና ጋርነር የኤቨርተንን የማሸነፊ ግቦች አስቆጥረዋል፡፡
በመጀመርያው ሳምንት በሊድስ የተሸነፈው የመርሲሳይዱ ክለብ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል፡፡
ክሪታል ፓላስ ከ ኖቲንግሀም ፎረስት ያደረጉት ጨዋታ ደግሞ አንድ አቻ ተጠናቋል፡፡ ኢስማኤል ሳር ለፓላስ ሆዱሶን ኦዶይ ደግሞ ለኖቶንግሀም ፎረስት ግቦቹን አስቆጥረዋል፡፡
 
 
በአንተነህ ሲሳይ