ማንችስተር ዩናይትድ ግብ ጠባቂው ሴኔ ላምመንስን ከሮያል አንትወርፕ ለማስፈረም ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡
ወደ ማንችስተር ለማምራት በግል ጉዳይ ስምምነት ላይ የደረሰው ቤልጀማዊው ግብ ጠባቂ ከቡድኑ ውጭ መሆኑን ዳይሊ ሜል ዘግቧል፡፡
የ23 አመቱ ግብ ጠባቂ ከስብስቡ ውጭ መሆኑ ወደ ማንችስተር ዩናይትድ የሚያመራበት ዕድል ሰፊ መሆኑን ማሳያ ሆኗል፡፡
በ17 ሚሊዮን ፓውንድ ወጣቱን ግብ ጠባቂ ማስፈረም የሚፈልገው ዩናይትድ ተጫዋቹ ጋር በግል ጉዳይ ቢስማማም ከሮያል አንትወርፕ ጋር ግን ገና በንግግር ላይ ይገኛል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ