Search

አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት ተገቢ ውክልና እንዲኖራት ሩሲያ ሙሉ ድጋፍ ትሰጣለች፦ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን

ሓሙስ ጥቅምት 19, 2019 46

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን አፍሪካ በተባበሩት መንግሥታት የጸጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምጽን በድምጽ የመሻር (ቬቶ) መብት ያላቸው ቋሚ መቀመጫዎችን ጨምሮ ተገቢው ውክልና እንዲኖራት ሩሲያ ሙሉ ድጋፍ እንደምትሰጥ አረጋገጡ።

በሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን፣ አፍሪካ በዓለም አቀፍ የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓቶች ውስጥ ተገቢውን ውክልና እንድታገኝ ሀገራቸው ሙሉ ድጋፍ ታደርጋልች ብለዋል።

በተለይም በተባበሩት መንግሥታት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ ድምፅን በድምፅ የመሻር (ቬቶ) መብት ያላቸው ቢያንስ ሁለት ቋሚ መቀመጫዎችን ማግኘት አለባት ብለዋል።

በተጨማሪም አምስት ጊዜያዊ ተለዋጭ አባላት ቦታዎችን እንድታገኝ የሚጠይቀውን የኤዙልዊኒ ስምምነት ሩሲያ ሙሉ በሙሉ እንደምትደግፍ በድጋሚ አረጋግጠዋል።

ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን አክለውም ሩሲያ እና የአፍሪካ ሀገራት ከርዕዮተ-ዓለም ጫና ነፃ በሆነ ባለብዙ-ዋልታ (Multipolar) የዓለም ሥርዓት ግንባታ ላይ አብረው እንደሚሠሩ ገልጸዋል።

አፍሪካውያን በዓለም አቀፍ መድረኮች ያላቸው ተሰሚነት እና ሚና ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን እና አሁንም ይበልጥ በተለያዩ መስኮች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

በጌቱ ላቀው

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: