የሩሲያ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን በሞስኮ እየተካሄደ በሚገኘው 3ኛው የሩሲያ - አፍሪካ ጉባኤ ላይ፣ ከፈረንጆቹ 2022 ወዲህ የሩሲያ እና የአፍሪካ ሀገራት የንግድ ልውውጥ በግማሽ አድጎ 27 ቢሊዮን ዶላር መድረሱን ገልጸዋል።
በሞስኮ በተካሄደው በዚህ ታሪካዊ ጉባኤ ላይ ፕሬዚዳንቱ የብሪክስ (BRICS) አባል የሆነችውን ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር በኢኮኖሚ፣ በኒውክሌር ኃይል ልማት፣ በግብርና እና በዲጂታል ቴክኖሎጂ ሽግግር ዙሪያ በቅርበት እየሠሩ መሆናቸውን አረጋግጠዋል።
በሁለቱ ወገኖች መካከል የሚደረጉ የንግድ ግብይቶች ከውጭ ጫና ነፃ በሆነ መልኩ በብሔራዊ ገንዘቦች የሚከናወኑ ሲሆን፣ የሩብል ድርሻም እስከ 85 በመቶ መድረሱን ጠቁመዋል።
ሩሲያ ለአፍሪካ ሀገራት የምታደርገው ድጋፍ ከጊዜያዊ ዕርዳታ የዘለለ አህጉሪቱ በራሷ አቅም ቆማ እሴት የምትጨምርበትን የኢንዱስትሪ እና የቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ያተኮረ መሆኑንም ፕሬዝዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ተናግረዋል።
በጌቱ ላቀው
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: