በ2ኛ ሳምንት የስፔን ላሊጋ ከሜዳ ውጭ ከሪያል ኦቪዶ የተጫወተው ማድሪድ 3 ለ 0 አሸንፏል፡፡
አሰልጣኝ ዣቢ አሎንሶ ሮድሪጎን ለመጀመርያ ጊዜ ቋሚ አድርጎ ባሳለፈበት ጨዋታ ኬይሊያን ምባፔ ሁለት ግቦችን አስቆጥሯል፡፡
ቪንሺየስ ጁኒየር ደግሞ 3ኛዋን ግብ ያስቆጠረ ተጫዋች ነው፡፡
ከ24 ዓመት በኋላ ወደ ላሊጋው የተመለሰው ሪያል ኦቪዶ በተከታታይ ለ2ኛ ጊዜ ተሸንፏል፡፡
ቪያሪያል ጂሮናን 5 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት አሸንፏል፡፡
በጨዋታው ቡቻናና ሦስት ግቦችን በማስቆጠር ሀትሪክ ሲሰራ ኒኮላ ፔፔ እና ራፋ ማሪን ቀሪዎቹን ግቦች አስቆጥረዋል፡፡
በሌሎች ዋታዎች ኦሳሱን ቫሌንሲያን 1 ለ 0 ሲያሸንፍ ሪያል ሶሲዳድ ከ ኢስፓኞል የተገናኙበት ጨዋታ ሁለት አቻ ተለያይተዋል፡፡
በአንተነህ ሲሳይ