Search

የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቭላዲሚር ፑቲን ከሞስኮው 3ኛው የሩሲያ-አፍሪካ ጉባኤ ላይ ያስተላለፏቸው ዋና ዋና መልዕክቶች፦

ሓሙስ ጥቅምት 19, 2019 73

ከፈረንጆቹ 2022 ወዲህ ኢትዮጵያን ጨምሮ ከአፍሪካ ሀገራት ጋር የሚደረገው የንግድ ልውውጥ በግማሽ አድጎ 27 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል።

የንግድ ግብይቶች ከውጭ ጫና ለመጠበቅ ሲባል በብሔራዊ ገንዘቦች (በሩብል) የሚከናወኑ ሲሆን፣ ድርሻቸውም እስከ 85 በመቶ መድረሱን አረጋግጠዋል።

የሩሲያ ኩባንያዎች ሀብት ዘርፎ ከመውጣት ይልቅ በሀገር ውስጥ እሴት እንዲጨምር፣ ፋብሪካዎች እንዲገነቡ እና የሥራ ዕድል እንዲፈጠር የሚያደርጉ መሆናቸውን አብራርተዋል።

አፍሪካ በዓለም አቀፍ የውሳኔ አሰጣጥ ሥርዓቶች ውስጥ፣ በተለይም በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ውስጥ የቬቶ መብት ያላቸው ቋሚ መቀመጫዎችን ጨምሮ ተገቢው ውክልና እንዲኖራት ሩሲያ ሙሉ ድጋፍ እንደምትሰጥ አረጋግጠዋል።

አፍሪካ ራሷን በምግብ እንድትመግብ ሩሲያ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ቶን እህል እና ማዳበሪያዎችን በየጊዜው በማቅረብ የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ አስተዋጽኦ እያበረከተች መሆኑ ተገልጿል።

በአሁኑ ወቅት በሩሲያ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ 40 ሺህ የሚጠጉ አፍሪካውያን ተማሪዎች እየተማሩ መሆኑን እና በሰው ሠራሽ አስተውሎት እንዲሁም በዲጂታል ቴክኖሎጂ ዘርፎች ትብብሩ እንደሚቀጥል ተመላክቷል።

 

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: