Search

በአሌክሳንደር ይሳቅ ዝውውር ያልተስማሙት ቡድኖች ያሚያደርጉት ጨዋታ:- ኒውካስትል ዩናይትድ ከሊቨርፑል

ሰኞ ነሐሴ 19, 2017 91

የ2ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ መርሀ ግብር ዛሬ በሚደረግ አንድ ጨዋታ ይጠናቀቃል፡፡
ምሽት 4 ሰዓት ላይ ኒውካስትል ዩናይትድ በሜዳው ከሊቨርፑል የሚገናኝበት ጨዋታ ይጠበቃል፡፡
በሊጉ መክፈቻ ቦርንማውዝን 4 ለ 2 ያሸነፈው ሊቨርፑል ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ከአስቶን ቪላ ነጥብ የተጋራው ኒውካስትል ዩናይትድ ደግሞ የመጀመርያ ሦስት ነጥቡን ለማግኘት የሚጫወቱ ይሆናል፡፡
በሴንት ጀምስ ፓርክ ስቴዲየም በሚደረገው ጨዋታ ወደ ሊቨርፑል መዛወር የሚፈልገው የኒውካስትል ዩናይትዱ አጥቂ አሌክሳንር ይሳቅ አሁንም ከስብስቡ ውጭ ሆኗል፡፡
ከሊቨርፑል ለሚደረገው ጨዋታ ስዊዲናዊው አጥቂ እንደማይኖር አሰልጣኝ ኤዲ ሀው ተናግረዋል፡፡
በይሳቅ እና በእሳቸው መካከል የተፈጠረ ነገር እንደሌለ የገለጹት አሰልጣኙ ተጫዋቹ በቅርቡ ወደ ቡድኑ ሊቀላቀል ይችላል ብለዋል፡፡
በተጠናቀቀው የውድድር አመት ከሙሀመድ ሳላ በመቀጠል በ23 ግቦች ከፍተኛ አስቆጣሪ ሆኖ በጨረሰው በአሌክሳንደር ይሳቅ ጉዳይ የተፋጠጡት ሁለቱ ቡድኖች ለአሸናፊነት ምሽት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡
በሌላ በኩል የኒውካስትል አዲሱ ፈራሚ ጃኮብ ራምሴ የመጀመርያ ጨዋታውን ሊያደርግ ይችላል ተብሏል፡፡
በሊቨርፑል በኩል ደግሞ የጡንቻ መሳሳብ ጉዳት የገጠመው ጀርሚ ፍሪምፖንግ ለተወሰኑ ሳምንታት በጉዳት የማይሰለፍ ተጫዋች ሆኗል፡፡
ኒውካስትል ዩናይትድ ባለፉት 17 የፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ሊቨርፑልን ማሸነፍ አልቻለም፡፡
በአንተነህ ሲሳይ

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ

ተያያዥ ዜናዎች: