Search

የውስጥ አቅምን በመጠቀም በጎነትን የሁልጊዜ ተግባር ማድረግ ያስፈልጋል - ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ

ሰኞ ነሐሴ 19, 2017 54

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሀገራዊ ብልጽግና ያለው ድርሻ ከፍ እንዲል የባህል እጥፋት ማምጣት እንደሚያስፈልግ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጥላሁን ከበደ ተናገሩ።

ርዕሰ መስተዳድሩ ይህንን የተናገሩት በክልሉ 1 ጀንበር 4600 ቤቶችን የማስገንባት መርግብር በወላይታ ሶዶ ከተማ ባስጀመሩበት ወቅት ነው።

ኢትዮጵያውያን ወገናቸውን ለመርዳት የውጭ ድጋፍ ብቻ መጠበቅ የለባቸውም ያሉት ርዕሰ መስተዳድሩ፥ የውስጥ አቅምን በመጠቀም በጎነትን የሁልጊዜ ተግባር በማድረግ የባህል እጥፋት ማምጣት ያስፈልጋል ሲሉ አሳስበዋል።

በአንድ ጀንበር ዘመቻ የሚጀመሩ ቤቶች በጥራትና በፍጥነት እንዲገነቡ አስፈላጊው ድጋፍ ይደረጋል ያሉት ደግሞ የርዕሰ መስተዳድር /ቤት ኃላፊ ዱጼ ታምሩ ናቸው።

የወላይታ ሶዶ ከተማ ከንቲባ እታገኝ ኃይለማርያም በበኩላቸው፤ በከተማዋ 130 ዜጎችን ተጠቃሚ የሚያደርግ የበጎ ፈቃድ አገልገሎት በክረምት ወራት እየተከናወነ እንደሚገኝ ገልጸዋል።

የዕድሉ ተጠቃሚ የሆኑት / ነገሰች ዎልቃ፥ ቤታቸው በተለይ በክረምት ወቅት ዝናብ የሚያስገባ በመሆኑ ተቸግረው መቆየታቸውን አስረድተው ድጋፍ ያደረጉ አካላትን አመስግነዋል።

በተመስገን ተስፋዬ