Search

የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ መንደር ከመኖሪያ ቤት ባለፈ የኢኮኖሚ አቅም ግንባታ ማዕከል ነው

ሰኞ ጥቅምት 23, 2019 57

የመደመር መንግሥት የከተማ ልማት መጪውን ዘመን ለትውልድ ማዘጋጀትን፣ የዜጎችን የኑሮ እና አኗኗር ዘይቤ ለመቀየር እና ለማሻሻል አቅሞቻችንን ደምረን መሥራት እንደሚገባ ያመላክታል።

ይህንን መርህ በተግባር ከሚያሳዩ ፕሮጀክቶች መካከል የቦሌ ሹቡ ኤጀርሳ የተቀናጀ ነዋሪዎች መንደር አንዱ ነው። ይህ መንደር የመኖሪያ ቤት ብቻ ሳይሆን የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ፣ የሥራ ዕድልና የማኅበራዊ አገልግሎት ማዕከል እንዲሆን ተደርጎ ተዘጋጅቷል።

ይህ የተቀናጀ የነዋሪዎች መንደር፦

 ዘመናዊ መኖሪያ ቤቶችን የያዙ ሁለት ጂ+4 ሕንፃዎችን፣ 

 የወተት ላሞችን መያዝ የሚችሉ የወተት ላም ማርቢያ ሼዶችን፣

 የእንስሳት መኖ ማቀነባበሪያን ከማሽኑ ጋር፣

 የንግድ ሱቆችን፣

 ዘመናዊ የግብርናና የፍጆታ ምርቶች ማከፋፈያና መሸጫ መጋዘንን፣

 የኤሌክትሪክ የእህል ወፍጮዎችን፣              

 ለጎልማሶች እና ወጣቶች የስፖርት ማዘውተሪያ፣

 የሕፃናት መጫወቻና ማቆያ ማዕከል፣ 

 የመሰብሰቢያ አዳራሽ ተገንብተዋል።

ከዚህ ፕሮጀክት ልዩ ትርጉም አንዱ አርሶ አደሮች ከቀድሞ የኑሮ ሁኔታቸው ጋር በተቀራረበ ግን ደሞ ዘመናዊ በሆነ መልኩ የእንስሳት እርባታና የወተት ምርት ሥራቸውን እንዲቀጥሉ፣ ቀጣይነት ያለው የገቢ ምንጭ እንዲኖራቸው መሠረት መጣሉ ነው።

ይህ ደግሞ የልማት ተነሺዎችን በተለየ እይታ የሚያይ፣ ከመኖሪያ ቤት ባለፈ የኢኮኖሚ አቅማቸውንና የማኅበራዊ ሕይወታቸውን በአንድነት ለማሻሻል የሚያስችል አካሄድ ነው።

የከተማ ልማት ትርጉም ያለው ዜጎች የተሻለ መኖሪያ፣ የገቢ ዕድል፣ ምቹ አካባቢና የተሻለ የነገ ተስፋ ሲያገኙበት ነው።

የዛሬና የነገው ልማታችን የነገውን ትውልድ የሚያበቃ እና የዜጎችን ኢኮኖሚያዊ ነፃነት የሚያጠናክር ሆኖም እንደሚቀጥል የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: