Search

ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ጥሪ የተደረገላቸው 23 ተጫዋቾች

ሰኞ ጥቅምት 23, 2019 47

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ለ2027 አፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ የምድብ ሦስተኛ እና አራተኛ ጨዋታዎቹን አርብ ሕዳር 4 በስታዲዮ ናሲዮናል ዶ ዚምፔቶ እንዲሁም ማክሰኞ ሕዳር 8 በባህር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከሞዛምቢክ ብሔራዊ ቡድን ጋር ያደርጋል።

አሰልጣኝ ዩሐንስ ሳህሌ ቡድኑ ከሞዛምቢክ ጋር ለሚያደርገው የደርሶ መልስ ጨዋታ ለ23 ተጫዋቾች ጥሪ አቅርበዋል።

በምድብ አስር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የመጀመሪያ ሁለት ጨዋታዎቹን በሱዳን እና በሴኔጋል በተመሳሳይ 1 ለ 0 ተሸንፏል።

ኬኒያ፣ ኡጋንዳ እና ታንዛኒያ በጣምራ የሚያስተናግዱት አፍሪካ ዋንጫ ሰኔ ወር ላይ ይካሄዳል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: