Search

ኢትዮጵያዊ አብሮነት ከሚያጠናክሩ ጉዳዮች አንዱ የበጎ ፈቃድ ሥራ ነው - የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ

ሰኞ ነሐሴ 19, 2017 38

የኢፌዴሪ ባህል እና ስፖርት ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማት ጋር በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ሽርቆሌ ወረዳ የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎትን አስጀምረዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር ሸዊት ሻንካ በዚሁ ወቅት እንዳሉት፤ ኢትዮጵያዊ አብሮነት ከሚያጠናክሩ ጉዳዮች መካከል የበጎ ፈቃድ አገልግሎት አንዱ በመሆኑ ትኩረት መስጠት አለብን ብለዋል። 

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል 13 አቅመ ደካሞች የቤት ግንባታ፤ 2 ሺህ ተማሪዎች  ደግሞ የትምህርት ቁሳቁስ ድጋፍ ማድረጉን ገልጸዋል።

በባህል እና ስፖርት ዘርፉ የስፖርት ቤተሰቦች እና አርቲስቶች ሀገራዊ አጀንዳዎች ላይ ያላቸው ተሳትፎ ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም ሚኒስትሯ ገልጸዋል። 

የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተደድር አሻድሊ ሀሰን በበኩላቸዉ፤ ባለፉት ዓመታት በክልሉ የተከናወኑ የበጎ ፈቃድ ሥራዎች አበራታች ውጤት እንዳመጡ አንስተው ለበርካታ አቅማ ደካሞችም እረፍት የሰጠ ነው ብለዋል። 

በክልሉ በተለያዩ አካባቢዎች በክልል መስሪያ ቤቶች ብቻ፤ 200 በላይ ቤቶች በዘንድሮው የበጎ ፈቃድ አገልግሎት እንደሚሰሩም ገልፀዋል። 

የበጎ ፈቃድ አገልግሎት የመደጋገፍ እና የአብሮነታችን መገለጫ ሆኖ እንደሚቀጥልም ርዕሰ መስተዳድሩ ጠቁመዋል።

በነስረዲን ሀሚድ