የትምህርትን አገልግሎትን ከገንዘብ ጋር ብቻ መያያዝ ሀገርን እንደሚጎዳ የትምህርት ሚኒስትር ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ተናገሩ።
በኢትዮጵያ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ አስፈላጊነትን በተመለከተ በትምህርት ሚኒስቴር በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።
የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትን ከሀገር ፍላጎት ጋር በማጣጣም በዓለም ነባራዊ ሁኔታ በመቃኘት መገንባት እንደሚገባም ነው የትምህርት ሚኒስትሩ በዚህ ወቅት የተናገሩት።
የትምህርት ተቋማት ለሀገር ግንባታ ገንቢ ሚና እንዲጫወቱ እና ወደፊት እንዴት መሄድ እንደለባቸው መግባባት ያሻል ብለዋል።
በኢትዮጵያ በትምህርት ሥርዓቱ ያለውን ችግር ለማጥራት ጥረቶች እየተደረጉ ቢሆንም፤ ጉዳዩን በታሰበው ፍጥነት መፍታት አለመቻሉንም ጠቁመዋል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያዘጋጀው የዳግም ምዝገባ፤ ተቋማት የተፈቀደውን የተማሪ እንየዲያስተምሩ፣ በራሳቸው ህንፃ ወይም ሙሉ ህንፃ ተካራይተው በምቹ ሁኔታ እንዲያስተምሩ፣ ተቋማት ሰነዶቻቸውን በአዲሱ መመሪያ መሰረት እንዲከዉኑ፣ የአሰራር ሥርዓቶችንና መዋቅሮችን እንዲከልሱ፣ የመምህራን ቅጥርን እንዲያሟሉ እንዲሁም ለማህበረሰብን ጠቃሚ ጥናትና ምርምር እንዲሰሩ ያስችላል ተብሏል።
ዳግም ምዝገባው በተቋማቱ የሕዝብ እምነት ለመገንባት ግልፅነት፣ ተጠያቂነት ለማስፈን ብሎም የጠራ ሙሉ መረጃ እንዲኖራቸው ለማድረግ እንደሚያግዝ ተገልጿል።
በላፉት ወራት በግል ተቋሟት ሲካሄድ የቆየው ጥናት ቀርቦ ውይይት እየተካሄደበትም ይገኛል።
በላሉ ኢታላ