Search

የገንዘብ ሚኒስትር ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) በአንታሊያ የኮፕ31 (COP31) ጉባኤ ጎን ለጎን ከUNDP አስተዳዳሪ ጋር ሁለትዮሽ ውይይት አደረጉ

ዓርብ ኅዳር 04, 2019 82

በአንታሊያ እየተካሄደ ባለው የኮፕ31 (COP31) ጉባኤ ጎን ለጎን የገንዘብ ሚኒስትር እና የኮፕ32 (COP32) ዋና ድርድር መሪ  ፍፁም አሰፋ (ዶ/ር) ከተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም (UNDP) ኃላፊ ከአሌክሳንደር ዲ ክሮ ጋር ሁለትዮሽ ውይይት አድርገዋል።

በውይይታቸውም ኢትዮጵያ ከድርጅቱ ጋር በአየር ንብረት ለውጥ እና በዘላቂ ልማት ዙሪያ ላላት የረጅም ጊዜ ትብብር ሰፊ ግምገማ አድርገዋል።

ውይይቱ ዋና ትኩረቱን በአየር ንብረት ፋይናንስ፣ በኢንቨስትመንት፣ በጽናት አቅም ግንባታ እና የኢትዮጵያን የአየር ንብረት እና የልማት ቅድሚያ የሚሰጣቸውን ጉዳዮች ትግበራ ለመደገፍ በሚደረጉ ጥረቶች ላይ ያደረገ ነበር።

በተጨማሪም በሁለቱ አካላት መካከል ያለውን ቀጣይ የትብብር ግንኙነት ይበልጥ ለማጠናከር በሚያስችሉ ዕድሎች ላይ መክረዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: