Search

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከሩዋንዳ ሪፐብሊክ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ጋር ተወያዩ

ሓሙስ ኅዳር 03, 2019 105

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር)፣ ከሩዋንዳ ሪፐብሊክ የአካባቢ ጥበቃ ሚኒስትር ዶ/ር በርናዴት አራክዊዬ ጋር ለCOP32 ዝግጅት ትብብርን ለማጠናከር ሁለትዮሽ ውይይት አካሂደዋል።

ሁለቱ ወገኖች በጋራ ቅድሚያ በተሰጣቸው ጉዳዮች ላይ በቅርበት ለመሥራትና ለሁሉም አካላት ትርጉም ያላቸው ውጤቶችን የሚያስገኝ የተሳካ COP32 እንዲኖር ጥረቶቻቸውን ለማስተባበር ተስማምተዋል።

የሰው ዘር መገኛ፣ የፅናት እና የተስፋ ምድር የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን አየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ የምታደርገውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሙሉ እና ትክክለኛ የጉባኤውን መረጃዎች ከምንጩ ለማግኘት ሁልጊዜም የኮፕ-32 ይፋዊ ድረ-ገጽ https://cop32ethiopia.et/ ይጠቀሙ።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: