በCOP31 የመሪዎች ጉባኤ ሁለተኛ ቀን፣ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የCOP32 ተመራጭ ፕሬዚዳንት ጌዲዎን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ከካሊፎርኒያ ገዢ ጋቪን ኒውሰም ጋር ተገናኝተው ተወያይተዋል። ገዢው ኢትዮጵያ የCOP32 አዘጋጅ ሀገር ሆና በመመረጧ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት የሀገሪቱን ቀጣይ የአየር ንብረት ተነሳሽነቶች አድንቀዋል።
በተጨማሪም በንጹህ ኃይል፣ በዘላቂ ትራንስፖርት እና በአረንጓዴ ፖሊሲዎች ዙሪያ ልምዶቻቸውንና ግንዛቤዎቻቸውን በመለዋወጥ፣ የአየር ንብረት እርምጃን ለማጠናከር የትብብር አስፈላጊነትን አጉልው ተወያይተዋል።
የሰው ዘር መገኛ፣ የፅናት እና የተስፋ ምድር የሆነችው ኢትዮጵያ ዓለም አቀፉን አየር ንብረት ጉባኤ ለማስተናገድ የምታደርገውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ በተመለከተ ሙሉ እና ትክክለኛ የጉባኤውን መረጃዎች ከምንጩ ለማግኘት ሁልጊዜም የኮፕ-32 ይፋዊ ድረ-ገጽ https://cop32ethiopia.et/ ይጠቀሙ።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: