በመርካቶ የበጎነት መንደር/በቅጠል ተራ የተገነቡት ዘጠኝ የመኖሪያ ቤት ሕንፃዎች ከተራ የግንባታ ሥራ በላይ፣ የዜጎችን የኑሮ ሁኔታ የሚቀይሩ፣ የቤተሰቦችን ተስፋ የሚያድሱና የማኅበራዊ ፍትህን በተግባር የሚያረጋግጡ የመደመር መንግሥት ቁርጠኝነት ማሳያዎች ናቸው።
የቤት ችግርን መቅረፍ ማለት የአንድን ቤተሰብ ነገ መገንባት፣ የልጆችን የተሻለ ዕድል ማረጋገጥ፣ የኑሮ ደኅንነትን ማጠናከርና የአካባቢውን ማኅበራዊና ኢኮኖሚያዊ ኑሮ ማነቃቃት ነው።
በመሆኑም ይህ ልማት ከአንድ ቤት ባለቤት መፍጠር በላይ የሚሄድ ማኅበራዊ እሴት አለው።
ዜጎች በተሻለ የኑሮ ሁኔታ እንዲኖሩ፣ ቤተሰቦች በኢኮኖሚያዊ ጫና ሳይገደቡ የወደፊት ዕቅዳቸውን እንዲያሳኩ፣ ማኅበረሰቡም በመተሳሰብና በአንድነት እንዲጠናከር የሚያግዝ ተጨባጭ ለውጥ ነው።
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከመደመር መንግሥት የከተማ ልማት ትግበራ ጋር በመዋሃድ፣ የዜጎችን ፍላጎት የመመለስ ቁርጠኝነቱን በተግባር እያሳየ ነው።
ቃልን በተግባር እያረጋገጠ ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የነዋሪዎችን ኑሮ እና አኗኗር ለማሻሻል በ24/7 በልዩ ትኩረት እየሰራ አንደሚገኝ የከተማ አስተዳደሩ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት መረጃ ያመላክታል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: