ህገ-ወጡ የሕወሓት ቡድን በትግራይ ሕዝብ ላይ የፈጸመው ጥፋትና ያስከተለው የፈተና ጊዜ እጅግ ከባድ ነበር። ይሁን እንጂ ዛሬ የትግራይ ሕዝብ ከዚህ የጥፋት አዙሪት በመውጣት ለሰላም እና ለልማት አዲስ ምዕራፍ ከፍቷል።
በተለይ የዓዲጉደም ከተማ ነዋሪዎች፣ “የዓዲጉደም ከተማ ወጣቶችና ሕዝብ ለልማት እንጂ ለጥይት አልተፈጠሩም!” በማለት ያሰሙት ድምፅ ህገ-ወጡን ቡድን በቁርጠኝነት የሚቃወም የሕዝብ ድምፅ ማስተጋቢያ ሆኗል።
የፌደራል መንግሥት የባለደራ አስተዳደር አቋቁሞ የሰላም አየር እንዲሰፍን በማድረጉም በከተማዋ በርካታ አበረታች ለውጦች መታየት ጀምረዋል።
ይህ የሰላም አየርና የነዋሪዎች ቁርጠኝነት በመቐለ ከተማም በድምቀት እየተንጸባረቀ ይገኛል። ከተማዋ ከነበረችበት ቀውስ በመውጣት ወደ መደበኛ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሴና ልማት ተመልሳለች።
ምንም እንኳን ብዙ መሰረተ ልማቶች ቢወድሙም ነዋሪዎቹ ሳይበገሩ የወደሙ ትምህርት ቤቶችን፣ የጤና ተቋማትን እና የአገልግሎት መስጫዎችን በድጋሚ ለመክፈትና ለመጠገን ከፍተኛ ጉጉትና ቁርጠኝነት እያሳዩ ነው።
በመልሶ ግንባታ ስራው የመሪዎችና የባለሙያዎች ሚናም የላቀ ነው።
በትግራይ ክልል የባለአደራ አስተዳደር የመቐለ ከተማ ከንቲባ ሺሻይ አማረ (ዶ/ር)፣ የሕዝቡን የልማት ጥማት እንደ ትልቅ አቅም በመውሰድ መንግሥት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ ይገኛል ብለዋል።
በተለይም የጤና ባለሙያዎች በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ ሳይቀር አገልግሎት ሳያቋርጡ በቁርጠኝነት መስራታቸው ያላቸውን ከፍተኛ ሙያዊ ታማኝነትና ሰብአዊነት የሚያሳይ ነው።
ሰላምና ጸጥታን ዘላቂ ለማድረግ ሕብረተሰቡ ጥፋትንና ሁከትን የሚሹ አካላትን እንቅስቃሴ በመከታተልና ጥቆማ በመስጠት ንቁ ተሳትፎ እያደረገ መሆኑ ተገልፃል ።
በልዩ እሸቱ
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: