Search

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ዛሬ በይፋ ያስመረቁት የኮሪደር ልማት ምን ምን መሰረታዊ ነገሮችን ይዟል?

ረቡዕ ኅዳር 09, 2019 69

የመደመር መንግሥት የከተሜነት ራዕይ:

ከተሞችን የሥራ ፈጠራ፣ የንግድ፣ የዕውቀትና የባህል ማዕከላት በማድረግ ለሕዝብ ቁጥር ዕድገትና ለአየር ንብረት ለውጥ ዘላቂ ምላሽ መስጠት።

57 ሄክታር የሚሸፍን አዲስ የኮሪደር ልማት: 

በቦሌ መድኃኔዓለም፣ እንግሊዝ ኤምባሲ፣ ሞኤንኮ፣ አደይ አበባ፣ ሻላ ፓርክ፣ ቺቺኒያ፣ ቦሌ ሩዋንዳ እና የውስጥ ለውስጥ መንገዶችን በማካተት በይፋ ተጀምሯል።

ዘመናዊና አረንጓዴ መሠረተ ልማት:

ሰፋፊ የእግረኛና የብስክሌት መንገዶች፣ የመሬት ውስጥ መሠረተ ልማቶች፣ የኤሌክትሪክ መኪና ቻርጅ ማድረጊያ ጣቢያዎች እና ከ5,000 በላይ ተሽከርካሪዎችን የሚይዙ ማቆሚያዎችን ያካትታል።

ሰውን ማዕከል ያደረጉ ማኅበራዊ አገልግሎቶች:

የታደሱ ትምህርት ቤቶች፣ ቤተ መጻሕፍት፣ የስፖርት ሜዳዎች፣ የመጫወቻ ሥፍራዎች፣ ካፌዎች፣ ሬስቶራንቶችና ፕላዛዎች ለዜጎች የኑሮ ጥራትና ክብር ተገንብተዋል።

ለመጪው ትውልድ የተነደፈ ዘላቂ ልማት:

ከመንገድ ግንባታ ባለፈ ምርታማ፣ አካታች፣ አረንጓዴ እና የማይበገሩ ከተሞችን ለመጪው ትውልድ የማስረከብ ትልቅ ራዕይ አካል ነው።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: