Search

ታሪክን እያከበርን፣ ማንነትን እያጠናከርን፣ ዐሻራን ለትውልድ እያስተላለፍን እንቀጥላልን፡- ከንቲባ አዳነች አቤቤ

ሓሙስ ኅዳር 10, 2019 39

ታሪክን እያከበርን፣ ማንነትን እያጠናከርን፣ ዐሻራን ለትውልድ እያስተላለፍን እንቀጥላልን ሲሉ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ ታሪክን በልማት ማስቀጠል፤ ዐሻራን ለትውልድ ማስተላለፍ! በሚል በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፣ ከተማ የምትገነባው በመንገድና በሕንፃ ብቻ አይደለም፤ ታሪኳን የሠሩ፣ ለሀገር ውለታ የዋሉ ባለውለታዎቿን በክብር በማስቀጠልም ጭምር ነው ብለዋል።

በአደይ አበባ ስታዲየም አካባቢ የኢትዮጵያን እና የአፍሪካን ስፖርት በማሳደግ ታላቅ ዐሻራ ያሳረፉትን ይድነቃቸው ተሰማን የሚዘክር ሐውልት መገንባታችን ከዚህ  እሳቤ የተነሳ መሆኑን አመላክተዋል።

ይድነቃቸው ተሰማ የአፍሪካ እግር ኳስ አባት፤ ይገባዋል ያሉት ከንቲባ አዳነች፣ እንደዚሁም ለሀገርና ለትውልድ አስተዋፅኦ ያበረከቱ ታላላቅ ሰዎችን መዘከር ታሪክን ከዛሬ ልማት ጋር በማስተሳሰር ለነገ ትውልድ ኩራትና መነሳሻ ይፈጥራል ብለዋል።

ልማት የዛሬን ከተማ ብቻ አይገነባም፤ የነገን ታሪክም ይጽፋል በማለት ገልጸው፣ ታሪክን እያከበርን፣ ማንነትን እያጠናከርን፣ ዐሻራን ለትውልድ እያስተላለፍን እንቀጥላልን ሲሉም አብራርተዋል።

አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: