በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ሁለተኛ ሳምንት ብርቱ ፉክክር በታየበት ጨዋታ ሊቨርፑል ኒውካስትልን 3 ለ 2 አሸንፏል።
ከሜዳቸው ውጭ ኒውካስትልን የገጠሙት ሊቨርፑሎች በመጀመሪያው አጋማሽ በ37ኛ ደቂቃ ግራቨንበርች ባስቆጠረው ግብ 1 ለ 0 እየመሩ ወደ መልበሻ ክፍል አምርተዋል።

የኒውካስትሉ የአጥቂ መስመር ተጫዋች አንቶኒ ጎርዶን የጨዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ ሊጠናቀቅ 45ኛው ደቂቃ ላይ በሊቨርፑል የተከላካይ መስመር ተጫዋች ቪርጅል ቫን ዳይክ ላይ በሠራው ጥፋት በቀጥታ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
ሊቨርፑሎች ከእረፍት መልስ በ46ኛው ደቂቃ በሁጎ ኤኪቲኬ አማካኝነት 2ኛዋን ግብ አስቆጥረው 2 ለ 0 መምራት ጀመሩ።
አንድ ሰው የጎደለባቸው ኒውካስትሎች ግን ጨዋታውን ተጭነው በመጫወት ብሩኖ ጉማሬሽ በ57ኛው ደቂቃ እና ዊሊያም ኦሱላ በ88 ደቂቃ ባስቆጠሯቸው ግቦች አቻ ሆነው የጨዋታውን ድባብ የመቀየር ደረጃ ላይ ደርሰው ነበር።
ሆኖም አስደናቂ ፉክክር በታየበት በዚህ ጨዋታ ተቀይሮ የገባው የ16 ዓመቱ የሊቨርፑል ተጫዋች ሪዮ ንጉሞሐ በ100ኛ ደቂቃ ባስቆጠራት ግብ ሊቨርፑሎች ሦስት ነጥብ አግኝተው መውጣት ችለዋል።
በዮናስ በደሉ