26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ 10 ኪሎ ሜትር የሩጫ ውድድር እሁድ ህዳር 13 2019 ዓ.ም የሚካሄድ ሲሆን ውድድሩን በማስመልከት ዛሬ ጋዜጫዊ መግለጫ የሰጡት የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ ታላቁ ሩጫ ከጎዳና ሩጫ ባሻገር ዘርፈ ብዙ ፋይዳ ያለው ወሳኝ ስፖርታዊ ኩነት ነው ብለዋል ።
ሚኒስትሯ መዲናችን አዲስ አበባ በአዳዲስ የኮሪደር ልማቶች ደምቃና ተውባ ለምትውልበት ለዚህ ታላቅ የስፖርትና የቱሪዝም ድግስ ለመላው ተሳታፊዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል።
በዓለም አትሌቲክስ ዕውቅና የተሰጠው ይህ ታላቅ ውድድር፣ እስካሁን የአፍሪካ ትልቁ የጎዳና ላይ ሩጫ ሆኖ መቆየቱን ያነሱት ሚኒስትር ሰላማዊት፤ አሁን ደግሞ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቁ የ10 ኪሎ ሜትር ውድድር እንዲሆን ለተጀመረው ጥረት የዘንድሮው ውድድር ትልቅ አቅም የሚፈጥር መሆኑን አስገንዝበዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የኢትዮጵያን የአትሌቲክስ ልዕልና፣ የእንግዳ ተቀባይነት ባህል እና የመዲናዋን ዘመናዊ የከተማ ገጽታ ለዓለም የሚያስተዋውቀው 26ኛው ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ በመጪው እሁድ በደማቅ ሁኔታ ይካሄዳል።
በውድድሩ ታሪክ 60 ሺህ ተሳታፊዎች በአዲስ አበባ ጎዳናዎች ላይ ይሮጣሉ ተብሎ ይጠበቃል።
አስተያየትዎን እዚህ ያስፍሩ: