ዛሬ በተደረገው የሴቶች 10 ሺህ ሜትር ፍጻሜ አትሌት ጉዳፍ ጸጋይ 3ኛ ወጥታለች፡፡
የቡዳፔስት ዓለም ሻምፒዮና የርቀቱ የወርቅ ሜዳልያ አሸናፊ ጉዳፍ ጸጋይ ለሀገሯ የነሀስ ሜዳልያ አስገኝታለች፡፡
የርቀቱ ዓለም ክብረ ወሰን ባለቤት ኬንያዊቷ ቢያትሪስ ችቤት ውድድሩን በአንደኝት አጠናቃለች፡፡
ጣልያናዊቷ አትሌት ባቶቼቲ ደግሞ 2ኛ ደረጃን በመያዝ የብር ሜዳልያውን ወስዳለች፡፡
በአንተነህ ሲሳይ