ሕፃናት ጤናማ አካላዊ እና አዕምሯዊ ዕድገት እንዲኖራው ወሳኝ ከሆኑ ነገሮች አንዱ ጤናማ የአመጋገብ ሥርዓት ነው።
በእርግዝና ወቅት ከእናትየው አመጋገብ ጀምሮ ሕፃን ተወልደው 2 ዓመት እስኪሆነው የሚሰጠው ምግብ በአካሉም ሆነ በስብዕናው ላይ የሚኖረው ተፅዕኖ ወሳኝ መሆኑን የሥነ-ምግብ ሕክምና ባለሙያዋ ኬብሮን ሰናይ ትገልፃለች።
ሕፃናት የተመጣጠነ ምግብ አግኝተዋል የሚባለው ውሃ መጠጣትን ጨምሮ የተለያዩ የእህል ዓይነቶች፣ አትክልት እና ፍራፍሬ እንዲሁም የእንስሳት ተዋፅዖ በአግባቡ ሲመገቡ መሆኑን ባለሙያዋ አብራርታለች።
ለሕፃናት ምግብ በሚዘጋጅበት ወቅት በዚያ ምግብ ውስጥ የተለያዩ ይዘቶችን እና ንጥረ ነገሮችን በማካተት እንዲመገቡ ማድረግ እንደሚገባም ነው ባለሙያዋ ያመላከተችው።
ለሕፃናት ምግብ በምናበስልበት ወቅት ዘይትን ሳይበዛ በመጠኑ መጠቀም እንዳለብን የጠቆመችው ባለሙያዋ፤ አያይዛም የጋለ ዘይትን በቅድሚያ መጠቀም ከጤና አንፃር አይመከርም ብላለች።
በንፍታሌም እንግዳወርቅ
#EBCdotstream #kids #nutrition #balanceddiet