Search

ብሪክስ እና ጂኦፖለቲክስ:- በዓለም አቀፍ ደቡብ ገበያዎች ውስጥ ያሉ ስልታዊ ዕድሎች

ማክሰኞ መስከረም 06, 2018 79

የዓለም ኢኮኖሚ ሥርዓት እየተቀየረ ስለመሆኑ ብዙ አስረጂዎችን ማቀርብ በሚቻልበት ሁኔታ ውስጥ ነው ያለነው በአሜሪካ የሚጣሉ የጉምሩክ ቀረጥና ከሌሎች ሀገራት ጋር ሳይመከር የምትወስዳቸው የንግድ ፖሊሲዎች ነባሩ የንግድ መስመሮችን እያወኩ መሆኑ የአደባባይ ሀቅ ሆኗል::

በዓለም አቀፍ ደቡብ ያሉ ሀገራትም ራሳቸውን ለመከላከል ስልታቸውን መቀየር እንዳለባቸው እየተረዱ ነው። ከብሪክስ አባላት መካከል ሁለት በጣም ተለዋዋጭ ኢኮኖሚ ያላቸው ሀገሮች ህንድ እና ብራዚል ይህን አዲስ አቅጣጫ እየመሩ ናቸው።

በሃይል ሽግግር፣ በዲጂታል ፈጠራ እና በመድሃኒት ዘርፎች ላይ ያተኮረው ጥምረታቸው ኢንቨስተሮች በንግድ ነፃነት ባላቸው ገበያዎች ውስጥ የሚፈልጉትን እድል የሚያሳይ አብነት ሆኗል::

ከአውሮፓውያኑ 2024-2025 አሜሪካ በብራዚል እና በህንድ ምርቶች ላይ 50 በመቶ ቀረጥ መጣሏ በተቃራኒው ስልታዊ ለውጥ እንዲፈጠር እና ይህም ለውጥ እንዲፋጠን አግዟል ይላሉ ባለሞያዎች

ሁለቱም ሀገራት በምዕራባውያን ገበያዎች ላይ ከመጠን በላይ ከመደገፍ በመጠንቀቅ፣ አሁን በብሪክስ ትብብር ላይ ትኩረት ሰጥተዋል።

የብራዚል ፕሬዚዳንት ልዩ አማካሪ ሴልሶ አሞሪም የአሜሪካ የጥበቃ ፖሊሲከብሪክስ ጋር ያለንን ግንኙነት እያጠናከረ ነውሲሉ በግልጽ ተናግረዋል።

የህንድ መንግሥትም በንግድ ውጥረት ውስጥስልታዊ ነፃነቷንአጽንዖት ሰጥታለች። ይህ ለውጥ የመከላከል እርምጃ ብቻ ሳይሆን የዓለም አቀፍ የንግድ ግንኙነትን እንደገና የመወሰን ንቁ ጥረት ነው።

በተለይም በህንድ እና በብራዚል መካከል ያለው ትብብር ፍጥነትን አግኝቷል። በሐምሌ 2025 ጠቅላይ ሚኒስትር ናሬንድራ ሞዲ ብራዚልን በጎበኙበት ወቅት ሁለቱ ሀገራት በአምስት ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ የተመሠረተ የትብብር መሪ ዕቅድ አውጥተዋል። እነዚህም መከላከያ፣ የምግብ ዋስትና፣ የሃይል ሽግግር፣ ዲጂታል ሽግግር እና የኢንዱስትሪ ትብብር ናቸው።

ህንድ እና ብራዚል በታዳሽ ኃይል ዘርፍ ከፍተኛ ዕድገት እያሳዩ ነው። በአውሮፓውያኑ 2024 የብራዚል የፀሐይ ኃይል ማመንጨት 75 ቴራዋት በሰዓት (TWh) ደርሷል፣ ህንድ ደግሞ 133 ቴራዋት በሰዓት (TWh) አምርታለች።

ሁለቱም ሀገራት በብሪክስ አዲስ ልማት ባንክ (NDB) የሚደገፉ ሲሆን፣ ለንጹህ ሃይል ፕሮጀክቶችም የገንዘብ ድጋፍ ያገኛሉ።

በተጨማሪም ሁለቱ ሀገራት በዲጂታል ቴክኖሎጂ ትብብር ላይ ተስማምተዋል። የህንድ  ዲጂታል ህንድ ፕሮግራም እና የብራዚል ዲጂታል መሠረተ ልማት (DPI) አቀራረብ እየተጣመረ ነው። በአውሮፓውያኑ 2025 የተፈረመ ስምምነት የሁለቱን ሀገራት የዲጂታል መፍትሄዎች፣ ለምሳሌ የአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና ብሎክቼይን (blockchain) የመሳሰሉትን፣ በጋራ ለመጠቀም ያለመ ነው።

ህንድ እና ብራዚል የወሰዱት አቅጣጫ ለአሜሪካ የንግድ ፖሊሲዎች ምላሽ ብቻ ሳይሆን፣ የዓለም አቀፍ ንግድን እንደገና የማሰብ ስልታዊ እርምጃ ነው። በሃይል ነፃነት፣ በዲጂታል ሉዓላዊነት እና በጤና ዋስትና ላይ ትኩረት በማድረግ፣ ከውጭ ድንጋጤዎች ተጋላጭነታቸው ያነሰ ኢኮኖሚ እየገነቡ ነው። ይህ ለኢንቨስተሮች ያልተለመደ ዕድልን ይፈጥራል።

በሰለሞን ገዳ