የኢትዮጵያ ሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት "በአዲሱ ዓመት ሰላም የሰፈነባት ኢትዮጵያ" በሚል መሪ ሀሳብ የሰላም ጉባዔ እያካሄደ ነው።
የምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት አሕመድ ሁሴን፤ አዲሱ ዓመት የጥይት ድምፅ የማይሰማበት የሀሳብ ልዩነቶች በውይይት የሚፈቱበት ብቻ ሳይሆን ተግባራዊ እርምጃ የምንወስድበት ሊሆን ይገባል ብለዋል።
ለዚህም ሀገር በቀል እውቀቶችን ፣ ባሕላዊ ሽምግልናዎችን ከዘመናዊው መፍትሄዎች ጋር አጣጥሞ መጠቀም እንደሚገባም አሳስበዋል።
በውይይቱ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።

በሰላም ጉባኤው ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል የወከሉ ተሳታፊዎች የሚያነሷቸው የመፍትሄ ሀሳቦች በሀገሪቱ ዘላቂ ሰላምን ለማምጣት ለሚደረገው ጥረት በግብዓትነት እንደሚያገለግሉም ተገልጿል።
በዚህ ሀገር አቀፍ የሰላም ጉባኤ ሀገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ የመንግስት ተቋማትና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
በአስማረ ብርሃኑ