የመቻል ምልክታችን የሆነው ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ነገ ለሚገጥመን አሉታዊ ነገር ሁሉ እንደምንችል የምናሳይበት ትርክታችን ነው ሲሉ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ምሁሩ ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ገለፁ።
ብሩክ ከድር (ዶ/ር) ከኢቲቪ ጋር በነበራቸው ቆይታ፤ ሕዳሴን ያለማንም ጣልቃ ገብነት ያሳካነው ፕሮጀክት ነው ብለን ለነገው ትውልድ የምናስተላልፈውን ታሪክ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
"ግድቡ ከኃይል ማመንጫነት ባለፈ ትርክት የምንፈጥርበት መሳሪያችን ነው ያሉት ምሁሩ፤ እንደ ሀገር ተባብረን ከሰራን ትልቅ ነገር ማሳካት እንደምንችል ታይቷል" ብለዋል።

የግድቡ መጠናቀቅ የነበሩ ቁጭቶችን በተግባር የሻረ መሆኑንም አንስተዋል።
ሕዳሴ የውጭ ጫናዎችን እና የታሪክ እጥፋቶችን በማለፍ በጋራ ድል ያደረግንበት ፕሮጀክት ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ሕዳሴ የኢትዮጵያውያን የማንሰራራት ምልክት ነው ያሉት ምሁሩ፤ በቀጣይም የልማት ራዕዮችን የምናሳካበት ተጨማሪ ድሎች ማስመዝገብ ይኖርብናል ብለዋል።
በሜሮን ንብረት