ኢትዮጵያውያን በጋራ ራዕይ በአንድነት በመቆም ስብራቶቻችንን ለይተን መፍትሄ ማበጀት፣ መጠገን ይገባናል ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ገለጹ።
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ዕድገት ስብራት ዋነኛ መንስዔ የጠላቶቻችን አጀንዳ የሆነው መለያየት ነው ሲሉም ተናግረዋል።
ጠላቶቻችን እኛን በዘር፣ በሐይማኖት፣ በሰፈር፣ በመንደር … በመለያየት አንድነታችንን ያፈርሳሉ፤ ለዚህ መድኃኒቱ መደመር ነው ብለዋል።
እኛ መደመር ስንል ጠላቶቻችን ይደነግጣሉ፣ ምክንያቱም እኛ ስንደመር ታላቅ ገድል እንደምንሠራ ከታሪካችን ያውቃሉና ነው ያሉት።
ኢትዮጵያውያን በጋራ መቆም ብንችል መፍጠን፣ መፍጠር እንዲሁም ከተከታይነት እና ተቀባይነት መላቀቅ እንችላለን ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በመደመር መንግሥት መጽሐፍ ምረቃ ላይ ተናግረዋል።
በሔለን ተስፋዬ