Search

ምሁራን የመደመር መንግሥት መፅሐፍን በተገቢው መንገድ ይተቹት - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

ረቡዕ መስከረም 07, 2018 37

የመደመር መንግሥት መፅሐፍ ሲጠቃለል 'ዛሬ ላይ ሆኜ ነገን ፤ነገ ላይ ሆኜ ዛሬን በምልልስ እና በምናብ እየቃኘሁ፤ እየተጋሁ እና እየሰራሁ ለልጆቼ የተሻለ ዓለም መፍጠር እችላለሁ' ብሎ የሚያምን መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡
ሐሳብ ያላችሁ ሰዎች መፅሐፉን የሚቃረን ነገር ፅፋችሁ ብታቀርቡልን ለማንበብ ብቻ ሳይሆን ለመማር ፤ ከመማርም ባሻገር የእናንተ ሃሳብ ይልቃል ብለን ለመመስከርም ጭምር ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡
የመደመር መንግሥት መፅሐፍም ሆነ የፃፈው ሰው ሙሉ አለመሆናቸውን አስቦ ትክክለኛ ሂስ ማቅረብ እንደሚቻልም አስረድተዋል።
ምሁራን ተቹት ፤ በተቃረነ መንገድ ሀሳብ ማፍለቅ የምትችሉ ሰዎች ሀሳብ አፍልቁበት ብለዋል።
ነገር ግን ሐሳብ አልቦ በሆነ መንገድ እንዴት እና መቼ ተፃፈ? ብላችሁ የምትቸገሩ ሰዎች ቢያንስ ቢያንስ ያልነውን እንደምንፈፅም፣ የጀመርነውን እንደምንጨርስ ፣ የምንናገረውን እንደምንፅፍ እንዲሁም የምንፅፈውን እንደምንኖር ኢትዮጵያውያን ይገነዘባሉ ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ተናግረዋል።
 
በንፍታሌም እንግዳወርቅ