ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ መጠናቀቁን አስመልክቶ በሶማሌ ክልል ጅግጅጋ ከተማ የድጋፍ ሰልፍ ተካሂዷል።
በድጋፍ ሰልፉ ላይ ንግግር ያደረጉት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሀመድ፤ የታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ ሀገራዊ መግባባትን ያጎለበተ ታላቅ ፕሮጀክት ነው ብለዋል።
የሕዳሴ ግድብ በሀገራችን የተጀመረውን የልማት እና የብልጽግና ጉዞ ለማፋጠን የሚያግዝ በመሆኑ የፕሮጀክቱን መጠናቀቅ በጉጉት ሲጠባበቅ ለነበረው መላው ኢትዮጵዊ ታላቅ የምስራች እንደሆነ አንስተዋል።
ግድቡ ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ እስኪጠናቀቅ ድረስ በርካታ የውስጥ እና የውጭ ፈተናዎች አጋጥመዋል ያሉት አቶ ሙስጠፌ፤ ነገር ግን በጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በሳል አመራር እና በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ያልተቋረጠ ድጋፍ ለፍፃሜ በቅቷል ብለዋል፡፡
የሕዳሴ መጠናቀቅ እኛ ኢትዮጵያውያን እንደ ሕዝብ አንድ ላይ ስንቆም ታሪክ መስራት እንደምንችል ያሳየንበት ትውልድ ተሻጋሪ የልማት አሻራችን ነው ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ገልፀዋል።
በሃብተሚካኤል ክፍሉ