ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ የትስስር ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሑፍ፤ የስንዴ እና የሩዝ ልማት 'አብዮት' በሚባል ደረጃ በአጭር ጊዜ እየተስፋፋ እና እየለማበት ለሚገኘው የሶማሌ ክልል ሕዝብ የሕዳሴ መጠናቀቅ በትጋት ታሪክን መቀየር እንደሚቻል ማሳያ ሆኖለታል ብለዋል።
በሶማሌ ክልል ያለው እምቅ ፀጋ በመደመር እሳቤ ለሀገር እና ለትውልድ አሻራን ለማኖር ትልቅ አቅም መፍጠር የሚችል ነው ሲሉም አስፍረዋል።
የሕዳሴ ግድብ መጠናቀቅን ተከትሎ ዛሬ በክልሉ ያየነው የድጋፍ ሰልፍ በርትቶ ለመስራት፣ ልማትን ለማስቀጠል እና ብልጽግናን ለማረጋገጥ ስንቅ የሚሆን ነው ብለዋል፡፡
በክልሉ በተለያዩ ከተሞች የተስተጋቡት መልዕክቶች መንግስትና ሕዝብ ለኢትዮጵያ ማንሠራራትና የከፍታ ጉዞ እጅ ለእጅ ተያይዘው መትመማቸውን በግልፅ ያሳዩ የልማት ቋንቋዎች ናቸው ሲሉ ገልጸዋል።