የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በሐረር ከተማ በ540 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚገነባውን 2ኛ ደረጃ ሞዴል ትምህርት ቤት ግንባታ አስጀመሩ።
መንግሥት የትምህርት ተደራሽነትን እና ጥራትን ይበልጥ ለማጎልበት በትኩረት እየሰራ ይገኛል ብለዋል ሚኒስትሩ።

በትምህርት የታገዘ እና በዕውቀት የበለጸገ ሀገር ተረካቢ ትውልድ የማፍራቱ ጥረት ተጠናክሮ ይቀጥላል ሲሉ ተናግረዋል።
የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በበኩላቸው፤ ባለፉት ዓመታት በክልሉ በትምህርት ዘርፍ በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤት መገኘቱን ገልጸዋል።
የትምህርት ጥራት እና ተደራሽነትን ለማጎልበት የሚገነባው ሞዴል ትምህርት ቤት የጎላ ጠቀሜታ እንደሚኖረው ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል።
በተያያዘ በሐረሪ ክልል በትምህርት ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት ላስመዘገቡ ተማሪዎች፣ እና ትምህርት ቤቶች እና ወረዳዎች በየደረጃቸው የማበረታቻ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በቴዎድሮስ ታደሰ